ራዕይ, ተልዕኮ እሴቶች ራዕይ, ተልዕኮ እሴቶች

ራዕይ

በ2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ዘመናዊ የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት ተደራሽ ሆኖ ማየት፡፡

ተልዕኮ

የመንገድ ትራንስፖርት ዘርፍ የልማት አጋሮችን በማስተባበር፣ በመደገፍና በመቆጣጠር፣ የትራንስፖርት ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን በስራ ላይ በማዋል ቀልጣፋ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ደህንነቱና ምቾቱ የተጠበቀ የትራንስፖርት አገልግሎት ህብረተሰቡ እንዲያገኝና ትራንስፖርት ለአገሪቷ እድገት የሚጠበቅበትን ሁሉ እንዲያበረክት ማድረግ፡

የባለስልጣኑ ዓላማዎች
  • ቀልጣፋ፣ ብቁ ፣ኢኮኖሚያዊና የተመጣጠነ የትራንስፖርት ሲስተም እንዲስፋፋ ማድረግ፣
  • የትራንስፖርት አገልግሎት ደህንነቱ የተጠበቀና ምቾት ያለው መሆኑን ማረጋገጥ፣
  • ብሔራዊና ዓለም አቀፍ የትራንስፖርት አገልግሎት መሥመሮች እንዲዘረጉና እንዲደራጁ ማድረግ እና
  • ትራንስፖርት በማንኛውም ረገድ እንዲያድግ ማበረታት ናቸው፡፡
ዕሴቶች
  • የተገልጋቻችን እርካታ የስኬታችን መለኪያዎች ናቸው
  • በጠንካራ የሥራ ተነሳሽነትና በቡድን ስሜት እንሠራለን
  • ባለድርሻ አካላት ወሳኝ አጋሮቻችን ናቸው
  • ህብረተሰቡ በመንገድ ትራንስፖርት እጥረት የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ፍላጎቱ እንዳይገታ እንተጋለን
  • በሰውና በንብረት ላይ የመንገድ ትራፊክ አደጋ እንዳይደርስ እንጥራለን

ስለ ትራንስፖርት ባለስልጣን ስለ ትራንስፖርት ባለስልጣን