ዜና ዜና

የሀገሪቱን የወጪ ገቢ እንቅስቃሴ ቀልጣፍ፣ ምቹና ተወዳዳሪ እንዲሆን በኢ-ሰርቪስ አገልግሎት አማካኝነት ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ ጥረት እየተደረገ ይገኛል

 

የሀገሪቱን የወጪ ገቢ እንቅስቃሴ ቀልጣፍ፣ ምቹና ተወዳዳሪ እንዲሆን በኢ-ሰርቪስ አገልግሎት አማካኝነት ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ ጥረት እየተደረገ ይገኛል

የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ለጭነት ትራንስፖርት ኦፕሬተሮች፣ ስራ አስከያጆች እና የቦርድ አባላት በኢ-ሰርቪስ ሲስተም አጠቃቀም ላይ  የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ፡፡

ባለስልጣን መ/ቤቱ የሀገር ዉስጥና የድንበር ተሻገር የጭነት ትራንስፖርትን በማዘመን የሀገሪቱን የወጪ ገቢ እንቅስቃሴ ቀልጣፍ፣ ምቹና ተወዳዳሪ እንዲሆን በኢሰርቪስ አገልግሎት አማካኝነት ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

ቀደም ሲል የነበረዉ የኢ-ሰርቪስ አግልግሎት በአብዛኛዉ ማኑዋል ላይ የተመረኮዘ ሲሆን በተጨማሪም የተደራሽነት እና ሴንተራል ዳታ ሲስተም ችግር የነበረበት በመሆኑ  በአዲሱ የኢ-ሰርቪስ አገልግሎት ማሻሻል አስፈልጓል፡፡

አዲሱ የኢ-ሰርቪስ አገልግሎት   ከበፊቱ የተሻለ የሚያደርገዉ ኢንተርኔት ዳታ ሲስተምን የሚጠቀም በመሆኑ ነው፡፡ በዚህም  ተገልጋዮች ባሉበት ቦታ ሆነው የሚፈልጉትን አገልግሎት ለማግኘት ማህበራቶች እና ድርጅቶች የራሳቸዉን ዩዘር አካዉነት  ከፍተው ከሲስተሙ ጋር በማገናኘት  መጠቀም እንዲችሉ ያደርጋል፡፡

የትራንስፖርት ኦፕሬተሮች፣ ስራ አስከያጆች እና የቦርድ አባላት የዘርፉ ዋነኛ የባለድርሻ አካላት ስለሆኑ በሲስተሙ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ እና ለትግበራዉም  የራሳቸዉ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ለማድረግ  ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጅቷል፡፡

በወቅቱም የባለስልጣን /ቤቱ  ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከመጡ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ስለ ሲስተም  አስፈላጊነት እና አጠቃቀም ዙሪያ  ለተሳታፊዎቹ ገለፃ አድርጓል፡፡ የመድረኩ ተሳታፊዎችም በቀረበዉ  ሀሳብ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ሰጥተዋል፡፡

ከተሳታፊዎች ለተነሱት ጥያቄዎች የፌዴራል ትራንስፖርት የባለስልጣን የትራንስፖርት ዘርፍ /ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልበር ሸምሱ እና ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የመጡ ባለሙያዎች ተጨማሪ ገለፃና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የጭነት ትራንስፖርት ማህበራት እና ኦፕሬተሮች ቢሮአቸዉን ከማደራጀት ጀምሮ የኢንተርኔትና ለሲስተሙ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን እንዲያሟሉ የሚደረግ ሲሆን ባለሙያዎቻቸዉ የተግባር ስልጠና እንዲወስዱ  እየተደረገ ይገኛል፡፡

አገልግሎት ፈላጊ የትራንስፖርት ኦፕሬተሮች በተዘረጋዉ ሲስተም አማካኝነት አስፈላጊ የሆኑ  ሰነዶቻችን እስካን አድርገው በሲስተሙ ላይ በመጫን በአዲስ መልክ በመመዝገብ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማግኘት ይችላሉ፡፡

በዚህም መሰረት የጭነት ትራንስፖርት ማህበራት የማመልከቻ መስፈርቶች፣ የተሽከርካሪ ዝርዝር፣ ሊብሬ፣ ቃለ-ጉባኤ፣ የቢሮ ኪራይ፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ዉስጠ ደንብ እና የአባላት የስምምነት ፊርማ አሟልቶ መላክ ይኖርባቸዋል፡፡

የግል ትራንስፖርት ደርጅቶች የተሽከርካሪ ዝርዝር፣ ሊብሬ፣ የኢንቨስትመንት ፈቃድ፣ የቢሮ ኪራይ ዉል/ ካርታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የአክሲዮን ማህበራት  የተሽከርካሪ ዝርዝር፣ ሊብሬ፣ ፈቃድ፣የቢሮ ኪራይ ዉል/ ካርታ፣ የንግድና የምዝገባ ፈቃድ፣ መመስረቻ ፅሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ  መላክ ይኖርባቸዋል፡፡

ባለስልጣን መ/ቤቱ የተላከዉን ማመልከቻ እና የአገልግሎት ጥያቄ ከተመለከተ በሁዋላ የሰነዶችን ትክክለኛነት አረጋግጦ ምላሽ የሚሰጥ ሲሆን አገልግሎት ፈላጊዎች ክፊያ ለመፈፀምና ኦርጅናል ሰነዶቻቸዉን ለማሳየት ብቻ ወደ ተቋሙ የሚመጡ ይሆናል፡፡

በተከታታይ ለስምነት ቀናት የሚሰጠዉ ስልጠና ሂደት የቀጠለ ሲሆን የጭነት ትራንስፖረት የማህበራት፣ ኦፕሬተሮች እና ድርጅቶች  ሰራተኞች በቀጣይነት በሲስተሙ ዙሪያ የተግባር ስልጠና የሚወስዱ ይሆናል፡፡


የዜና ክምችት የዜና ክምችት