ዜና ዜና

ስልጠናው በፌደራልና በክልል ትራንስፖርት ቢሮዎች መካከል ያለውን የመረጃ ልውውጥ እንደሚያጠናክር ተገለጸ፡፡

NEWSየፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ለክልልና ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮዎች የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡

በወቅቱም የህዝብ ግንኙነት ሃላፊዎችና ባለሙያዎችን ሙያዊ ብቃት ሊያሳድጉ በሚችሉ በዜናና መጣጥፍ አጻጻፍ ”feature and news writing” እና ህዝብ ግንኙነትና ስነተግባቦት “public relation and communication” ርእሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የኮርፖሬት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሃንስ በቀለ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ለማድረስ በስልጠናው ያገኙትን ተጨማሪ እውቀት መጠቀም እንዳለባቸው ገልጸው ከሚዲያዎች ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት ለማጠናከር ፣ የተቋማቸውን መልካም ገጽታ ለመገንባት እና በትራንስፖርት ዘርፉ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ ጠንክረዉ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

NEWSተሳታፊዎቹ በበኩላቸዉ እንደገለጹት ስልጠናው ሙያዊ አቅምን የሚገነባ፣ በመረጃ ቅብብሎሽም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እርስ በርሳቸዉ እና የፌደራሉ ትራንስፖርት ባለስልጣን ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ እንደሚያሻሻል ገልጸው ወደ ፊት ተመሳሳይ መድረኮች ሊፈጠሩ ይገባል ብለዋል፡፡

ከስልጠናው በተጨማሪም የፌደራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ክፍሎች የ2010 ዓ.ም እቅድና የ1ኛ ሩብ አመት አፈጻጸማቸዉን አቅርበዉ ዉይይት አድርገዋል፡፡


የዜና ክምችት የዜና ክምችት