ዜና ዜና

መልካም ዜጋ የፍጥነት ወሰን ገደብን አያልፍም!

መልካም ዜጋ የፍጥነት ወሰን ገደብን አያልፍም!

ከጳጉሜ እስከ ጳጉሜ እንደርሳለንበሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሀ ግብሮች ሲካሄድ የነበረው የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ንቅናቄ መርሃ ግብር ጳጉሜ 5 ቀን 2012 . በላም በረት መናሀሪያ የፍጥነት ወሰን ገደብ መቆጣጠሪያ መሳሪያ ገጣሚ ተቋማት ባደረጉት አውደ ርዕይ ተጠናቋል፡፡

እለቱመልካም ዜጋ የፍጥነት ወሰን ገደብን አያልፍም”! በሚል መሪ ቃል የፍጥነት ወሰን ገደብ ቀን ሆኖ ተከብሮ ውሏል፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ / ሙሉ ገብረ እግዚአብሔርን ጨምሮ የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ያዴታ እና ሌሎች የባለስልጣኑ አመራሮችና በአውደ ርዕዩ ላይ ተገኝተዋል፡፡

ሚኒስቴር ዲኤታ / ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር እንደተናገሩት ቀጣዩ አመት የመንገድ ትራፊክ አደጋ የማናይበት አመት እንዲሆን አሽከርካዎችና ሌሎች አካላት የመንገድ ትራፊክ ህጎችን አክብረው መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የተሽከርካሪዎችን ፍጥነት ወሰን ለመገደብ የሚያስችል መሳሪያ በተሽከርካሪዎች ላይ ለማስገጠም ባለፈው አንድ አመት ጀምሮ ጊዜ ተሰጥቶት ሲሰራበት የቆየ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ አመት ይህን ተግባራዊ በማያደርጉ አካላት ላይ እርምጃዎች ስለሚወሰዱ ሁሉም አካል የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በአውደ ርዕዩ ላይ ስለ ተሽከርካሪ ፍጥነት ወሰን መገደቢያ መሳሪያ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች፣ በዘርፉ ስለተፈጠሩ የስራ እድሎች፣ ስለአጋጠሙ ችግሮችና ሌሎችም ጉዳዮች ለተሳታፊዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡                                

 


የዜና ክምችት የዜና ክምችት