ዜና ዜና

ኢትዮ የተሽከርካሪ አስመጪ ማህበር ለፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ሰራተኞች የማስክና ሳኒታይዘር ድጋፍ አደረገ

ኢትዮ የተሽከርካሪ አስመጪ ማህበር ለፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ሰራተኞች የማስክና ሳኒታይዘር ድጋፍ አደረገ

ኢትዮ የተሸከርካሪ አስመጪ ማህበር በዛሬው እለት ጳጉሜ 4 ቀን 2012 . የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ለተቋሙ ሰራተኞች የሚውል 245 ሺህ ብር የሚያወጣ የማስክና ሳኒታይዘር ድጋፍ አድርጓል፡፡

የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ መሐመድ አመዴ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት ድጋፉ የተደረገው የባለስልጣኑ ሰራተኞች ራሳቸውን ከኮቪድ 19 ጠብቀው አገልግሎት እንዲሰጡ ለማገዝ ነው ብለዋል፡፡ አቶ መሐመድ አክለውም የኢትዮ የተሸከርካሪ አስመጪ ማህበር ለሆስፒታሎች፣ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ለሚሰሩ ድርጅቶችና ለተለያዩ አካላት በዓይነትና በገንዘብ ድጋፎችን እንዳደረገ ገልፀው በቀጣይም ከመንግስት ጋር ተባብሮ ለመስራት ቁርጠኛ አቋም መያዙን ተናግረዋል፡፡

በድጋፍ ርክክቡ ላይ የተገኙት የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ያደታ ኢትዮ የተሸከርካሪ አስመጪ የተቋሙን አቅም ለማሳደግ ከተቋሙ ጎን ሆኖ ድጋፍ በማድረጉ ምስጋናቸውን ገልፀው የትራንስፖርት ዘርፍ ሰራተኞች ራሳቸውን ከወረርሽኙ እንዲጠብቁ ከተደረገ እነዚህ ሰራተኞች በስራ ጉዳይ የሚያገኙትን ተገልጋይም መታደግ እንችላለን ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በመንግስት በጀት ብቻ ሁሉንም ክፍተት መሸፈን ስለማይቻል ሌሎች የትራንስፖርት ማህበራት ከመንግስት ጎን በመቆም ችግሮችን በጋራ ለመፍታት መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡ ፡


የዜና ክምችት የዜና ክምችት