ዜና ዜና

ከአጠቃላይ ሰራተኛ ጋር ምክክር አካሄደ፡፡

ከአጠቃላይ ሰራተኛ ጋር ምክክር አካሄደ፡፡

የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ዙርያ ከአጠቃላይ የተቋሙ ሰራተኛ ጋር ምክክር አካሄደ፡፡

የአስር ዓመቱ የልማት እቅድ ዓላማ በዋናነት በዘርፉ ያለውን አገልግሎት በማሻሻል ሀገሪቱ ከድህነት ተላቃ መካከለኛ ገቢ ካላቸዉ ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ የበኩሉን አስተዋጾ እንዲያደርግ  የታሰበ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለዚህ ዓላማ መሳካትም በእቅዱ አበይት ተግባራት የተቀመጡ ሲሆን የትራንስፖርት መሰረተ ልማትን ተደራሽነት ከማረጋገጥ አንጻር በአገር አቀፍ ደረጃ የህዝብ ትራንስፖርት መናሀርያዎችን መገንባት፣ በገጠር መንገዶች  መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት ሽፋንን ማሳደግ ፣ የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎትን በማሻሻል ከ50ሺ በላይ  ነዋሪ የሚኖሩባቸዉ 69 ከተሞች ላይ  የብስክሌት  ትራንስፖርት አገልግሎትን ማስፋፋት  ፣ አዲስ  መስመሮችን በጥናት በመለየት   እንዲከፈቱ  ማድረግ ፣በትላልቅ ከተሞች ላይ የብዙሃን ትራንስፖርትን ማስፋፋት እና በአዲስ አበባከተማ  የትራንስፖርት መጠበቂያ ሰዓትን  አምስት  ደቂቃ ለማድረስ መስራት፣ የሚሉት በዋናነት ይገኙበታል፡፡

ከመድረኩ እንደተገለጸዉ በ2012 በጀት ዓመት በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ የተገለጸ ሲሆን በተለይ ዘርፉን ለማዘን ከቴክኖሎጂ ጋር የተያያዙ በርካታ ስራዎች መሰራታቸዉ ተገልጿል ፡፡

ከተከናወኑት ተግባራት መካከልም በበጀት ዓመቱ እያንዳንዱ ተሽከርካሪ ላይ ደረጃ በደረጃ  የፍጥነት መገደቢያ ማሽን እየተገጠመ መሆኑ፣ በዘርፉ የሚሰጡ አገልግሎቶች በኢ-ሰርቪስ  አማካይነት እየተሰጡ መሆናቸዉ እና  የኤሌክትሮኒክስ  ትኬት አገልግሎት  ለመጀመር ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቃቸዉ  ይገኙበታል ፡፡

የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር  አቶ አብዲሳ ያደታ በወቅቱ እንደገለጹት በዘንድሮ በጀት ዓመት የካፒታል በጀት ፐሮጀክቶች  በርካታ በመሆናቸዉ አመራሩም ሆነ ሰራተኛዉ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባዉ በመግለጽ ሌሎችም የታቀዱ ተግባራትን በአጭር፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ  በመለየት እና የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት በመጠቀም ማከናወን እንደሚገባ አሳስበዋል ፡፡


የዜና ክምችት የዜና ክምችት