ዜና ዜና

ከባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት ተካሄደ

 

                    ከባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት ተካሄደ

የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በ10ዓመቱ የልማት ዕቅድ ዙርያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት አካሄደ፡፡

በአስር ዓመቱ መሪ ዕቅድ ላይ የተለያዩ የተቋሙ ባለድርሻ አካላት በተለያዩ ጊዚያት ደረጃ በደረጃ ውይይት እንደተደረገበት  ከመድረኩ ተገልጿል፡፡

በወቅቱ በቀረበው የአስር ዓመት የልማት እቅድ ላይ በዋናነት ከተካተቱት ዉስጥ  የትራንስፖርት መሰረተ ልማትን ተደራሽነት ከማረጋገጥ አንጻር በአገር አቀፍ ደረጃ የህዝብ ትራንስፖርት መናሀርያዎችን መገንባት፣ በገጠር መንገዶች  መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት ሽፋንን ማሳደግ፣ የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎትን በማሻሻል ከ50ሺ በላይ  ነዋሪ የሚኖሩባቸዉ 69 ከተሞች ላይ  የብስክሌት  ትራንስፖርት አገልግሎትን ማስፋፋት፣ አዲስ  መስመሮችን በጥናት በመለየት   እንዲከፈቱ  ማድረግ ፣ በትላልቅ ከተሞች ላይ የብዙሃን ትራንስፖርትን ማስፋፋት እና በአዲስ አበባከተማ  የትራንስፖርት መጠበቂያ ሰዓትን  አምስት  ደቂቃ ለማድረስ መስራት   የሚሉት በዋናነት ይገኙበታል፡፡

በወቅቱ ከቀረበዉ እቅድ በመነሳት ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየት እና ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን ከጅቡቲ- አዲስ አበባ ያለው  መንገድ ብልሽት ምክንያት በሰዉ ሕይወት፣ በንብረት እና በተሸከርካሪዎች ምልልስ ላይ ከፍተኛ ችግር እየደረሰ መሆኑ፣ በህዝብ ትራንስፖርት ዘርፍ ልዩ ባሶች ለህብረተሰቡ ከፍተኛ አገልግሎት  እየሰጡ እንደሆነ ቢታወቅም  በቀረበዉ እቅድ ላይ የልዩ አውቶቢሶች  የተርሚናል ግንባታ ያልተካተተ ስለሆነ በ2013 በጀት ዓመት እቅድ ዉስጥ መካተት ቢችል ፣ አዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ ያሉ መናሀሪያዎች  ደረጃቸውን   የጠበቁ ባለመሆናቸዉ ለተጠቃሚዎች  ተገቢዉን  አገልግሎት እየሰጡ አይደሉም  የሚሉ ጥያቄዎች  እና ሌሎችም  ሀሳቦች ቀርበዋል፡፡

በመጨረሻም ለቀረቡት ጥያቄዎች ከመድረኩ እና ከሚመለከታቸዉ  የስራ ሀላፊዎች  ምላሽ የተሰጠበት ሲሆን በእቅዱ ያልተካተቱ ገንቢ አስተያየቶች በግብዓትነት  እንዲሚወስዱ ተገልጿል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 


የዜና ክምችት የዜና ክምችት