ዜና ዜና

የድንበር ተሻጋሪ የጭነት አሽከርካሪዎችን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል እንዲቻል የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

የድንበር ተሻጋሪ የጭነት አሽከርካሪዎችን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል እንዲቻል የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

ድጋፍ የተደረገው ገንዘብ እናቁሳቁ ስለ ኮሮና ቫይረስ መከላከል ብሄራዊ የድጋፍ አሳባሰቢ ኮሚቴ እና ለትራንስፖርት ሚኒስቴር የተሰጠ ነው፡፡ድጋፉ የቀረበውም በቶታል ኢትዮጵያ፣ በቪዥን ፈንድ ማይክሮ  ፋይናንስ፣ በኢትዮጵያ የትራንስፖርት አሰሪዎች ፌደሬሽን እና በኢትዮጵያ ባህረኞች ማህበር አማካይኝነት ነው፡፡

ድጋፍ የተደረገው ገንዘብ እና ቁሳቁስ ከኢትዮጵያ ጅቡቲ የጭነት እቃዎችን ለሚያመላልሰው አሽከርካሪዎች ለኮሮና ቫይረስ እንዳይጋለጡ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች ለመሰራት እንዲቻል ነው፡፡

የትራንስፖርት ሚንስቴር ሚንስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የህብረተሰቡን መሰረታዊ የሆኑ ጭነቶችን ወደ ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ወደ ውጪ በማጓጓዝ ቀዳሚ ድርሻ የሚወስደውን አሽከርካሪ ከኮሮና ቫይረስ መጠበቅ እንዲችል የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ላደረጉ ድርጅቶች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ አክለውም ለወገን ደራሽ ወገን በመሆኑ እርስ በራስ በመደጋገፍ ያሉ ብንን ጉድለቶች በመሙላት ቫይረሱ የሚያሳድረውን ተጽእኖ መቀነስ ይቻላል ብለዋል፡፡ በቀጣይም ተቋሙ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ድጋፋቸው እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የተደረገው ድጋፍ በቀጣይ ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርስ ወደ ደወሌ እና ጋለፊ ኬላ የሚጓጓዝ ይሆናል፡፡ ድጋፉ የቀረበው በገንዘብ እና በቁሳቁስ ሲሆን ከተደረጉት ቁሳቁሶችመካከል ጄኔሬተር፣ ፍሪጆች፣ ሳኒታይዘር ፣አልኮልእናማስክ ይገኙበታል፡፡

ድጋፉን ካደረጉ ድርጅቶች መካከል የቶታል ኢትዮጵያ ተወካይ እንደተናገሩት ድርጅታቸው በሀገሪቱለ ረጅም አመታት በነዳጅ አቅርቦት ላይ የተሰማራ መሆኑን ገልጸው በሽታው በሀገሪቱ ላይ የሚያደርሰውን ተጽእኖ ለመቀነስ የበኩላቸውን አስተዋጾ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡ እንደዚሁም የድርጅታቸው አሽከርካሪዎች ነዳጅ ለማጓጓዝ ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚንቀሳቀሱ በመሆኑ ራሳቸውን ከቫይረሱ እንዲጠብቁ አስፈላጊውን ቁሳቁስ እና ስልጠናዎች ለአሽከርካሪዎቻቸው እንደሚያቀርቡ አስታውቀዋል፡፡ እንደዚሁም የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌደሬሽን ተወካይ እንደገለጹት ከዛሬው ድጋፍ በፊት ለድንበር ተሻጋሪ የጭነት አሽከርካሪዎች ለኮሮና ቫይረስ እንዳይጋለጡ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም ደወሌ እና ጋላፊ ለሚሰራው የጭነት ተርሚናል ግንባታ የትርንስፖርት ሚንስቴርን እና የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣንን እንደሚያግዙ ገልጸዋል፡፡

የብሄራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ምስጋናው አረጋ ድጋፍ ያደረጉ ድርጅቶችን አመስግነዋል፡፡ አሁንም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በተለያዩ አማራጮች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 


የዜና ክምችት የዜና ክምችት