ዜና ዜና

የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የጭነት ትራንስፖርት ኦፕሬተር የአደረጃጀት ረቂቅ የመመሪያ ማሻሸያ ሰነድ ላይ ከጭነት ትራንስፖርተሮች ጋር ዉይይት አካሄደ፡፡

የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የጭነት ትራንስፖርት ኦፕሬተር የአደረጃጀት ረቂቅ የመመሪያ ማሻሸያ ሰነድ ላይ ከጭነት ትራንስፖርተሮች ጋር ዉይይት አካሄደ፡፡

በወቅቱም እንደተገለፀዉ ነባሩን መመሪያ ማሻሻል ያስፈለገበት አላማ የጭነት ትራንስፖርት ማህበራትን ወደንግድ ተቋም ለማሸጋገር ነው፡፡

በነባሩ የአሰራር መመሪያ የጭነት ትራንስፖርት ማህበራቱ በሚጠበቀው ደረጃ አለማደጋቸው፣ሀብትም ማፍራት ባለመቻላቸዉ እና በዘርፉ በቂ የሆነ ለዉጥ ባለመታየቱ ዘርፉን ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን ተገልጿል፡፡

በቀረበው የመጨረሻዉ ረቂቅ መመሪያ ላይ ዉይይት በማድረግ ተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየት እና ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡

ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ትጥያቄዎች በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የትራንስፖርት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልበር ሸምሱ እና መመሪያዉን ያቀረቡት ባለሙያዎች ሰፊ ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በወቅተም እንደተገለጸው በባለስልጣን መ/ቤቱ ላለፉት ሶስት አመታት ነባሩን የጭነት ትራንስፖርት ኦፕሬተር የአደረጃጀት ብቃት ማረጋገጫ መመሪያን ለማሻሻል ሰፊ ጥናት ስለመደረጉ የተገለፀ ሲሆን የጭነት ትራንስፖርተሮች እና የባለድርሻ አካላት ግብአት እንዲሰጡበትም ተደርጓል፡፡የዜና ክምችት የዜና ክምችት