ዜና ዜና

ኤሌክትሮኒክ አገልግሎት ኤሌክትሮኒክ አገልግሎት

የዳይሬክተሩ መልእክት የዳይሬክተሩ መልእክት

ዜናዎች እና ለውጦች ዜናዎች እና ለውጦች

የችግኝ ተከላ መረሀ ግብር ተካሄደ

የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ሰራተኞች በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሽዋ ዞን ሎሜ ጠዳ ወረዳ በመገኘት ችግኝ በመትከል አርንጓዴ አሻራቸውን አሰርፈዋል፡፡

የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አገልግሎት ሊጀመር ነዉ

የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የተከሰተዉን የኮረና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስና ንክኪን ለማስቀረት በመነሀርያዎች የሚሰራዉን የክፍያ ስርዓት ለማዘመን ከክፍያ ፋይናንሽያል ቴክኖሎጂ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና ከህዝብ ትራንስፖርት ማህበራት ጋር በመተባበር የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አገልግሎትን በይፋ አሰጀመረ ፡፡

የድንበር ተሻጋሪ የጭነት አሽከርካሪዎችን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል እንዲቻል የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

ድጋፍ የተደረገው ገንዘብ እናቁሳቁ ስለ ኮሮና ቫይረስ መከላከል ብሄራዊ የድጋፍ አሳባሰቢ ኮሚቴ እና ለትራንስፖርት ሚኒስቴር የተሰጠ ነው፡፡ድጋፉ የቀረበውም በቶታል ኢትዮጵያ፣ በቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናንስ፣ በኢትዮጵያ የትራንስፖርት አሰሪዎች ፌደሬሽን እና በኢትዮጵያ ባህረኞች ማህበር አማካይኝነት ነው፡፡

የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የጭነት ትራንስፖርት ኦፕሬተር የአደረጃጀት ረቂቅ የመመሪያ ማሻሸያ ሰነድ ላይ ከጭነት ትራንስፖርተሮች ጋር ዉይይት አካሄደ፡፡

በወቅቱም እንደተገለፀዉ ነባሩን መመሪያ ማሻሻል ያስፈለገበት አላማ የጭነት ትራንስፖርት ማህበራትን ወደንግድ ተቋም ለማሸጋገር ነው፡፡

የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል የሚያግዝ የድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሸከርካሪዎች ተርሚናል ግንባታ ተጀመረ

በሶማሌ ክልል በሽንሌ ሲቲ ዞን አይሻ ወረዳ ደወሌ ቀበሌ የሚገኘውን የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል የሚያግዝ የድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሸከርካሪዎች ተርሚናል ግንባታን በይፋ ተጀምሯል፡፡